Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ ከቻይና ቀይ መስቀል ማህበር 100 ሺህ የኮቪድ-19 ክትባት ሊረከብ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከቻይና ቀይ መስቀል ማኅበር የተደረገለትን 100 ሺህ የሲኖፋርም ኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ነገ ይረከባል፡፡
ማኀበሩ ከቻይና ቀይ መስቀል ማኀበር የተደረገለትን ድጋፍ በጤና ሚኒስቴር በኩል ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ለጤና ሚኒስትር ያስረክባል ነው የተባለው፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር ቀደም ሲል ለጤና ሚኒስቴርና ትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ የኮቪድ መከላከያ ቁሳቁሶችን፣ መድሃኒቶችን ለተቸገሩ ወገኖች፣ ለልዩ ልዩ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ጋዋኖችን፣ የእጅ ጓንቶችን፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአጠቃላይ 30 ሚሊየን ብር የሚጠጉ ቁሳቁሶችን ማስረከቡ ይታወቃል፡፡
እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የመከላከል ተግባራትንና ወረርሽኙ ተፅእኖ ላሳደረባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.