Fana: At a Speed of Life!

ኪንግደም ኢትዮጵያ ናይለን ኃ.የተ.የግ.ማህበር በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የናይለን ምርት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኪንግደም ኢትዮጵያ ናይለን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የናይለን ምርት ጀመረ፡፡
ኩባንያው በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገነባወ ፋብሪካ በቻይና ካለው እናት ፋብሪካው በሦስት እጥፍ የሚበልጥና ከአፍሪካም በናይለን ምርት ግዙፉ ፋብሪካ ያደርግዋል ተብሏል፡፡
ኩባንያው እስካሁን ለ300 ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ ለ1ሺህ ሠራተኞች ተጨማሪ የስራ ዕድልን መፍጠር እንደሚችል ተነግሯል ፡፡
ኪንግደም ኩባንያ በአሁኑ ወቅት የናይለን ክር ማምረቻ ከውጪ እያስገባ ቢሆንም ወደፊት ይህንኑ ግብአት ሙሉ ለሙሉ ከሀገር ውስጥ ለማግኘት እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ከኢንዱስትሪያል ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.