የሀገር ውስጥ ዜና

በወላይታ ዞን ምርጫ ለማካሄድ የሚደረገው ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

By Meseret Awoke

June 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚደረገው ዝግጅት መጠናቀቁን የወላይታ ምርጫ ማስተባበሪያ ዋና ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በዞኑ 13 የምርጫ ክልሎች 1ሺህ 20 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን፥ 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ ፡፡

ካሉት13 የምርጫ ክልሎች በሰባት የየምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንደሚካሄድና በስድስት ምርጫ ክልሎች ላይ ደግሞ ምርጫ እንደማይካሄድ የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ስምኦን አስታውቀዋል ፡፡

ምርጫውን ማካሄድ የሚያስችል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ምርጫ ወደሚካሄድባቸው ሰባት ወረዳዎች እየተሰራጨ እንደሚገኝና ወረዳዎችም ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የመጡ ቁሳቁሶቹን በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡

እንደወላይታ ዞን 13 የምርጫ ክልሎች 1ሺህ 20 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ ያሉት አስተባባሪው፥ ከነዚህ መካከል ምርጫው በ624 ጣቢያዎች በሰባት የምርጫ ክልሎች ምርጫው እንደሚካሄድ ተናግረዋል ፡፡

በምርጫው ከ1ሚሊየን በላይ ህዝብ መመዝገብ አለበት ተብሎ የታቀደ ሲሆን፥ ከ800ሺህ በላይ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቧል ፡፡

ምርጫ በሚካሄድባቸው በሰባቱ ምርጫ ክልሎች ከ600 ሺህ በላይ ህዝብ ይመርጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተገለጸ ሲሆን፥ ቀሪው መራጭ ህብረተሰብ በ2ኛው ዙር ድምፁን እንደሚሰጥ ተናግረዋል ፡፡

በዞኑ 12 የፖለቲካ ፖርቲዎች ከ340 በላይ እጩዎች ለክልል እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይወዳዳራሉ ፡፡

በማስተዋል አሰፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!