Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ማርቆስ ዮኒቨርሲቲ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ሸለመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ማርቆስ ዮኒቨርሲቲ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ሰጠ፡፡
ውጤታቸው ከ3 ነጥብ 75 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ 228 ተማሪዎች ናቸው የተማሪዎች አምባሳደር ለመሆን የሚያበቃ እውቅና የተቸራቸው።
ከእነኝህ ተማሪዎች መካከል 43 ያህሉ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
ዩኒቨርሲቲው ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር በተማሪዎች ዘንድ መልካም የሆነን የእርስ በእርስ የፉክክር መንፈስ እንዲኖር በማስቻል ከፍ ያለ ሚና እንዳለው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ ተናግረዋል።
በዛሬው እለት እውቅና ያገኙ ተማሪዎች በዮኒቨርሲቲው በሚደረጉ የምርምር ፕሮጀክቶችን በመንደፍና የመሳተፍ ሚና ይኖራቸዋል።
ተማሪዎቹ ለሰላማዊ መማር ማስተማርና ለትምህርት ጥራት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሎም ይጠበቃል።
በፕሬዚዳንት አምባሳደርነት ዝርዝር የተካተቱ ተማሪዎች በዮኒቨርሲቲው ዋናው ግቢና በቡሬ ካምፓስ ከ2ተኛ አመት በላይ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ናቸው።
በዚህ እውቅና ላይ 1ኛ ለወጡ ተማሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣2ተኛ ለወጡ ተማሪዎች ታብሌት፣ 3ተኛ ለወጡቱ ደግሞ የሞባይል ስልክ ተሸልመዋል።
በአወል አበራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.