በካፋ ዞን ለሚካሄደው ምርጫ ቁሳቁስ ደርሷል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በካፋ ዞን የፊታችን ሰኞ ለሚካሄደው ምርጫ ቁሳቁስ መግባቱን የዞኑ የምርጫ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገለፀ።
በዞኑ 8 የምርጫ ክልሎች 590 የምርጫ ጣቢያዎች እንዲሁም 13 ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ የገለፁት የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ አባተማም፣ 7 የፖለቲካ ፓርቲዎች 112 እጩዎችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት ማቅረባቸውን ተናግረዋል።
የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ መሆኑን አስተባባሪው ገልፀዋል።
በካፋ ዞን ካሉት 8 የምርጫ ክልሎች በ 7ቱ ምርጫ የፊታችን ሰኔ 14 እንደሚካሄድ ያስታወቁት አስተባባሪው በ1 የምርጫ ክልል ምርጫ የሚደረገዉ ጳጉሜ 1 ነው ብለዋል።
በካፋ ዞን ድምፅ ለመስጠት 524 ሺ 686 ሰዎች መመዝገባቸውን ያስታውሱት አስተባባሪው የፊታችን ሰኞ በ 7 የምርጫ ክልሎች ከ400 ሺ በላይ ዜጎች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በፍሬህይወት ሰፊው እና አለማየሁ መቃሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!