የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ ሸዋ ዞን የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

June 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን በምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተካሄደ ነው።

ስርጭቱ በዞኑ ድምፅ በሚሰጥባቸው 11 የምርጫ ክልሎችና 1 ሺህ 540 የምርጫ ጣቢያዎች ነው እየተካሄደ መሆኑን የምስራቅ ሸዋ ዞን የምርጫ ፅህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ደበሌ ወርቁ ተናግረዋል።

አክለውም የቁሳቁስ ስርጭቱ በተለያዩ ምክንያቶች ድምፅ የማይሰጥባቸውን 32 የምርጫ ጣቢያዎች እንደማይጨምር ጠቅሰዋል።

በዞኑ ከ1 ሚሊየን 18 ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!