Fana: At a Speed of Life!

በጂማ ዞን ለምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ተጠናቀው ደርሰዋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂማ ዞን ለ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ተጠናቀው መድረሳቸውን የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ሸሪፍ አባገላን እንዳሉት የምርጫ ቁሳቁስ ለሁሉም ምርጫ ክልሎች የደረሱ ሲሆን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማጓጓዙ ስራም እስከ ነገ 5 ሰዓት ድረስ ይጠናቀቃል ብለዋል።

በዞኑ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የግል ተወዳዳሪ ሲመዘገቡ፥ 33 እጩዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 68 ደግሞ ለክልል ምክር ቤት ይወዳደራሉ ተብሏል።

እንደ ሃላፊው ገለጻ 18 የምርጫ ክልል እና 1 ሺህ 583 የምርጫ ጣቢያ ላይ ድምፅ ለመስጠት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ተመዝግበዋል።

በሌላ መልኩ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ዜጎች ያለምንም ስጋት በምርጫው እንዲሳተፉ እየሠራሁ ነው ብሏል።

የመምሪያው ሀላፊ ኮማንደር ዲባባ ረጋሳ እንዳሉት የፀጥታ አካል ከምዝገባ ጀምሮ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ በቀጣይ ዜጎች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ወጥተው ይበጀኛል ያሉትን እንዲመርጡም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተያያዘም በጅማ ዞን በምርጫ እለት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አታውቋል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱን ለመከላከል በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ የጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ የሱፍ ሻሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።

በእለቱ የእጅ መታጠቢያ ውሃ፣ ሳሙናና ሳኒታዘር እንደ ሚቀርብና ህብረተሰቡ ርቀቱን ጠብቆ ድምፅ እንዲሰጥ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንም አንስተዋል።

በአፈወርቅ አለሙ እና ሙክታር ጠሃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.