ስፓርት

ኢትዮ አፍሪካ የአሰግድ ተስፋዬ የመታሰቢያ ውድድር አሸናፊ ሆነ

By Tibebu Kebede

June 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሰግድ ተስፋዬ የመታሰቢያ ውድድር በኢትዮ አፍሪካ የእግር ኳስ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡

የፍጻሜ ጨዋታው በኢትዮ አፍሪካ እና አበበ ቢቂላ ቡድኖች መካከል የተደረገ ሲሆን፥ መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜው አንድ ተጠናቋል፡፡

በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት ኢትዮ አፍሪካ 5 ለ 4 አሸናፊ ሆኗል።

ውድድሩ መጠናቀቁን ተከትሎም የውድድሩ ኮከቦች የተመረጡ ሲሆን፥ ቢኒያም ኃይሌ ከኢትዮ አፍሪካ ኮከብ ተጫዋች፣ ሚራጅ ነስረዲ ከኢትዮ አፍሪካ በአምስት ጎል ኮከብ ጎል አግቢ፣ ሳሙኤል ዳኜ ከኢትዮ አፍሪካ ኮከብ አሰልጣኝ እንዲሁም ውብሸት ደሳለኝ ከኢትዮ አፍሪካ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመሆን ተመርጠዋል፡፡

ኮተቤ እግርኳስ ማኅበር ደግሞ የስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ መሆኑን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!