የሀገር ውስጥ ዜና

በቤንች ሸኮ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተደርጓል

By Tibebu Kebede

June 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ማድረጉን የቤንች ሸኮ ዞን ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ሃላፊ ኮማንደር ዳዊት ጢሞቲዎስ ከምዝገባው ቀን አንስቶ ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።

ሰኞ የሚደረገው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅም በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ ፖሊስ መመደቡን ተናግረዋል።

የፀጥታ ችግር በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ፖሊስን ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በማቀናጀት ስምሪት መሰጠቱንም ተናግረዋል።

ለምርጫው በሰላም መጠናቀቅ ህብረተሰቡ የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በትብብር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን በሁለት የምርጫ ክልሎችና በ223 የምርጫ ጣቢያዎች አራት የፖለቲካ ፖርቲዎች ይፎካከራሉ።

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 8 እንዲሁም ለክልል ምክር ቤት ደግሞ 24 ዕጩዎች ይሳተፋሉ።

በዞኑ 215 ሺህ 766 ሰዎች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተስፋዬ ምሬሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!