ሃሰተኛ መረጃን ለመከላከል ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል – የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃሰተኛ መረጃ በተለይም በምርጫ ወቅት የሚያደርሰውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከል ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ምርጫን የተመለከቱ መረጃዎችን ከታማኝ ምንጮች በመከታተል ትክክለኛ መረጃን ለማግኘት ጥረት ማድረግ ይገባል ያሉት ነዋሪዎቹ፥ መገናኛ ብዙሃን ያለባቸውን ሃላፊነት ተግባር ላይ ማዋል እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡
መገናኛ ብዙሃን የተጣሩና ፈጣን መረጃዎችን በማድረስ ሃሰተኛ መረጃዎች የሚያስከትሉትን አደጋ ለመቀነስ መስራት እንደሚገባቸውም አብራርተዋል።
የፊታችን ሰኞ ለሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊነት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተመሳሳይ ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡
በደብረ ማርቆስ ከተማ 18 ያህል የምርጫ ጣቢያዎች እና 1 ሺህ 455 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ።
በምርጫ ቦርድ የምስራቅ ጎጃም ዞን ምርጫ አስተባባሪ አቶ ስለሺ ወርቅነህ፥ ምርጫውን ለማከናወን የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
ምርጫው በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በአወል አበራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!