የሀገር ውስጥ ዜና

በደሴ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ወደየምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ነው

By Tibebu Kebede

June 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ ለድምጽ መስጫ ማስፈጸሚያነት የሚያገለግሉ የምርጫ ቁሳቁስ ወደየምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጩ መሆኑን የከተማው የምርጫ ክልል ሀላፊ አስታወቁ።

የምርጫ ክልሉ ኃላፊ አቶ ዮሀንስ አሰፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ የሚሰራጨው የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ እሁድ ጠዋት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በተገኙበት ማለዳ 12 ሰአት ይከፈታሉ፡፡

በደሴ ከተማ የምርጫ ክልል 104 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ።

በምርጫ ክልሎቹ 82 ሺህ 177 መራጮች ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸውን የምርጫ ክልሉ ኃላፊ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በደሴ ከተማ ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ቀን እና ከምርጫ በኋላ አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ጽህፈት ቤት እና የከተማዋ የጸጥታ ሀይል ለፋና በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!