Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ቀይ መስቀል ማህበር 100 ሺህ የኮቪድ19 ክትባት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ቀይ መስቀል ማኅበር 100 ሺህ የኮቪድ19 ክትባት ለኢትዮጵያ ቀስ መስቀል ማኅበር አስረከበ።

ድጋፍ ከተደረገው 100 ሺህ ክትባት መካከል 40 ሺህ ለትግራይ ክልል የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ድጋፉን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን አስረክበዋል፡፡

አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን “ኢትዮጵያ የኮቪድ19 ወረርሺኝን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ቻይና ትደግፋለች” ብለዋል።

ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ድጋፍ ቻይና ማድረጓን ገልጸው ክትባቱ በርካታ ሰዎች ከወረርሺኙ ራሳቸውን እንዲከላከሉ ይረዳቸዋል ነው ያሉት።

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ቻይና ላደረገችው ድጋፍ አመስግነው ክትባቱ ወረረሺኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጎች የኮቪድ19 ክትባት መውሰዳቸውን ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.