በኢራን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ኢብራሂም ራይሲ አሸነፉ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢራን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ኢብራሂም ራይሲ አሸነፉ፡፡
ወግ አጥባቂ እንደሆኑ የሚነገርላቸውና በዳኝነትና ጠበቃነት ያገለግሉት ራይሲ በምርጫው 62 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡
ማሸነፋቸውን ተከትሎም በመጭው ነሐሴ ወር ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡
ራሳቸውን የፀረ ሙስና አቀንቃኝ አድርገው የሚገልጹት ራይሲ ከምዕራባውያን ተቃራኒ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡
ተመራጩ ፕሬዚዳንት በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባቸው ሲሆን፥ በፈረንጆቹ 1988 በቴህራን አቅራቢያ በሚገኝ ማረሚያ ቤት በሞት ከተቀጡ እስረኞች ጉዳይ ጋር በተያያዘም እጃቸው እንዳለበት ይነገራል፡፡
በወቅቱ የታራሚዎችን የፍርድ ሂደት የተመለከተውና በኋላም የሞት ፍርድ የበየነው የዳኞች ቡድን አባል በመሆን አገልግለዋል ነው የተባለው፡፡
በርካታ ኢራናውያን እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ታራሚዎቹ ላይ ለተበየነው “ሚስጢራዊ የሞት ቅጣት” ግለሰቡን ዋነኛ ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡
በሰአቱ ከቴህራን ወጣ ብሎ በሚገኝ ጥብቅ ማረሚያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የፖለቲካ እስረኞች መገደላቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ታራሚዎቹ ተቀብረውበታል የተባለው የጅምላ መቃብር ግን እስካሁን አለመገኘቱም ነው የሚነገረው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!