የሀገር ውስጥ ዜና

ፍቃድ ሳይሰጥ በሠርግ እና በተለያዩ ምክንያቶች ርችት እንዳይተኮስ ፖሊስ አሳሰበ

By Tibebu Kebede

June 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሠርግ እና በተለያዩ ምክንያቶች ፍቃድ ሳይሰጥ ርችቶችን መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በተለያዩ አካባቢዎች ካለፍቃድ የሚተኮሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ አንዳንድ ግለሰቦች በሕገ-ወጥ መንገድ የገዙትን የጦር መሣሪያ እንደሚፈትሹ እና የተለያዩ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ሁኔታዎች እያጋጠመ መሆኑን ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው ጥናቶች እና አሰሳዎች ማረጋገጡን አስታውቋል።

ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ እንደማይችልም ነው የገለጸው፡፡

ሁኔታው የከተማዋ የፀጥታ ስጋት እንዳይሆን ኅብረተሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ ለፖሊስ አባላት መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረቡን የኮሚሽኑ ነመረጃ ያመላክታል።

ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ፍቃድ ሳይሰጥበት ርችቶችን በሚተኩሱ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳልም ብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!