Fana: At a Speed of Life!

በምርጫ እለት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ቅድመ ዝግጅት አድርገናል – የጂማ ዞኑ ጤና ጽ/ቤት

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን በምርጫ እለት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ የሱፍ ሻሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።

በእለቱ የእጅ መታጠቢያ ውሃ፣ ሳሙናና ሳኒታዘር እንደ ሚቀርብና ህብረተሰቡ ርቀቱን ጠብቆ ድምፅ እንዲሰጥ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

በምርጫ እለትም ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፏል።

በዞኑ 18 የምርጫ ክልሎች ስር 1 ሺ 5 መቶ 83 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን፤አጠቃላይ 1 ሚሊየን 558 ሺህ 304 ሰዎች ተመዝግበው የምርጫ ካርድ ወስደዋል።

ከተመዝጋቢዎች መካከል 48 ነጥብ 1 በመቶ ሴቶች ናቸው።

በሙክታር ጣሃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.