የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመልካም ምኞት መግለጫ መርሐ-ግብር ተካሄደ
የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመልካም ምኞት መግለጫ መርሐ-ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመልካም ምኞት መግለጫ መርሐ-ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሄደ።
መርሐ-ግብሩ በማይንድ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ ሲሆን የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዘንድሮው ምርጫ ፉክክራቸው መልካም ምኞት ለመግለጽ ዓላማው ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ፥ዛሬ ምሽት ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች በማሰባሰብ የመልካም ምኞት መግለጫ ሥነ ሥርዓት ያዘጋጀውን “ማይንድ ኢትዮጵያ” እናመሰግናለን ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው።
በእርግጥም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ሲሉም አሰፍረዋል።
የመልካም ምኞቱ መግለጫ ላይ ተፎካካሪ የፖለተካ ፓርቲ አመራሮች፣ የምርጫ ቦርድ ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ አምባሳደሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!