የሀገር ውስጥ ዜና

በቻግኒ የምርጫ ክልል ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች ክረምትን ተከትሎ ዝናቡ መስተጓጎል እንዳይፈጥር ዝግጅት ተጠናቀቀ

By Meseret Awoke

June 20, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በቻግኒ ከተማ የምርጫ ክልል ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች ክረምትን ተከትሎ ዝናቡ መስተጓጎል እንዳይፈጥር ዝግጅት ተጠናቋል።

መራጮች ድምጽ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ሄደው በዝናብ ምክንያት ችግር እንዳይገጥማቸው፣ ማረፍ የሚችሉባቸው ድንኳኖች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን የማዘጋጀት ስራ መከናወኑን በምርጫ ጣቢያዎቹ ላይ ተገኝተን ታዝበናል።

ክዚህ ባለፈ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ ያለምንም የጸጥታ ስጋት መጠናቀቅ እንዲችል የጸጥታ አካሉ መዘጋጀቱንም ለመረዳት ችለናል።

የምርጫ ቁሳቁስን ወደየምርጫ ጣቢያዎች በሰላም እንዲደርሱ ከማጀብ አንስቶ በድምጽ መስጫው ዕለትም ምንም አይነት የጸጥታ ችግር እንዳይኖር ሁሉም የጸጥታ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጅቱ መጠናቀቁንም ተመልክተናል።

ዛሬ ተዘዋውረን የተመለከትናቸው ምርጫ ጣቢያዎች የመብራት እና ሌሎች ለምርጫው የሚያግዙ ቁሳቁሶችንም ዝግጁ ያደረጉ ናቸው።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!