በምርጫው ቅድመ ዝግጅት ላይ በመሳተፍ የበኩላችን እየተወጣን እንገኛለን – የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምርጫው ላይ በመገኘት ድምፅ ለመስጠት ከመዘጋጀት ባሻገር በቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
ለምርጫው በሚሆኑ የቦታ ዝግጅትና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ በተለይም በድንኳን ተከላና መሠል ተግባራቶች ላይ እየተሳተፉ እንደሆነም ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት፡፡
ነዋሪዎቹ በየአካባቢያቸው ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የተከላ ስራውንና ለምርጫ ሂደቱ አስፈላጊ የሚባሉ ተግባራቶችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
ከምርጫው ጋር በተያያዘም ድምፃቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን በመግለጽ፥ የሀገር ሰላም ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑም ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!