የሀገር ውስጥ ዜና

በአምቦ አንድ ምርጫ ክልል ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እየተደረገ ያለው ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው

By Meseret Awoke

June 20, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአምቦ አንድ ምርጫ ክልል ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እየተደረገ ያለው ዝግጅት እየተጠናቀቀ ይገኛል።

በምርጫ ክልሉ 94 ምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን፥ 69 ሺህ 696 መራጮች ተመዝግበዋል።

እስካሁን በተደረገው ዝግጅትም ምርጫውን ለማካሄድ የሚረዱ የምርጫ ቁሳቁሶችም በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ ።

ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሀሳባቸውን የሰጡ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች፥ መራጩ ህዝብ ካርዱን በመጠቀም ለሀገር ይበጃል ያለውን እንዲመርጥ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣም ነው ነዋሪዎቹ የጠየቁት።

በይድነቃቸው ኃ/ማርያም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!