Fana: At a Speed of Life!

ከምርጫው በኋላ የከተማችን ሰላም እናስቀጥላለን-የቢሻን ጉራቻ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀገራዊ ምርጫው በኋላ ከተማዋ በምትታወቅበት ሰላማዊነቷ እንድትቀጥል የበኩላቸውን እንደሚወጡ በኦሮሚያ ክልል የቢሻን ጉራቻ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ከ24 ሰዓታት ያነሰ ጊዜ ለቀረው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

በተለይም ፓርቲዎች በቅድመ ምርጫ ወቅት ያሳዩትን ጨዋነት የተላበሰ አካሄድ በምርጫው ዕለትም ሆነ ከምርጫው በኋላ ማስቀጠልና የምርጫ ውጤትን በጸጋ መቀበል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በተለይም አሁን ላይ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጥንቃቄ ከማድረግ አንጻር መዘናጋት ይስተዋላል ያሉት ነዋሪዎቹ÷ በምርጫው ሂደት ራሳችንንና ሌሎችን ከወረርሽኙ መጠበቅ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የቢሻን ጉራቻ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ቃሲም ቱንኢ ለምርጫው የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።

በምርጫ ክልሉ 4 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ 6 ሺህ ዜጎችም ድምፅ መስጠት የሚስችላቸውን የምርጫ ካርድ ወስደዋል፡፡

በምስክር ስናፍቅና ጥላሁን ይልማ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.