የሀገር ውስጥ ዜና

በቡታጅራ፣ መስቃን እና ማረቆ ወረዳ ስር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢዎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

June 20, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2013 ፣ (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት ለሚካሄደው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ በቡታጅራ ከተማ እና በመስቃንና ማረቆ ወረዳ ስር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢዎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተካሄደ ነው፡፡

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የመስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልል 87 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ ከነዚህ መካከል 27 ቱ በቡታጅራ ከተማ የሚገኙ ናቸው።

በዚህ የምርጫ ክልል 71 ሺህ 333 መራጮች ካርድ ወስደው የተዘጋጁ መሆናቸውን የክልሉ ምርጫ አስተባባሪ አቶ ብሩክ ነስሩ ተናግረዋል፡፡

የቡታጅራ ፖሊሲ ጽህፈትቤት አዛዥ ዋና ሳጅን ሙስጠፋ በድሩ በበኩላቸው ÷ የምርጫ ቁሳቁሱ ወደ ተመደበለት የምርጫ ጣቢያ እንዲደርስም ሆነ የመራጮችን ደንህነት ለመጠበቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን አረጋግጠዋል፡፡

በኬነሳ አመንቴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!