Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊነት አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ወደ ስራ ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ፖሊስ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊነት አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግና በቂ የሰው ሃይል በመመደብ ወደ ስራ መግቱን አስታወቀ፡፡
ለህብረተሰቡ ስጋት የሆኑ ወንጀሎችን ለመከላከልም ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡
በየምርጫው ጣቢያው የሚጓጓዙ የምርጫ ቁሳቁሶች አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ እና እስካሁን በከተማዋ ያለው እንቅስቃሴ ፍፁም ሰላማዊ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም ለ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቅ የበኩሉን ሚና በመወጣት አጋርነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በየምርጫ ጣቢያው እና በሁሉም የከተማው አካባቢዎች ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በአካል በመሄድ ማሳወቅ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ 0115526303 ነፃ ጥሪ 987 ፣አዲስ አበባ ፖሊስ 011-1 11-01-11 ነፃ የስልክ ጥሪ 991 ፣ቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 0116674618፣አዲስ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 0112733743፣ኮልፌ ቀራንዮ ፖሊስ መምሪያ 0113717753፣ን/ስ/ላፍቶ ፖሊስ መምሪያ 0114431529፣አራዳ ፖሊስ መምሪያ 0111573426፣ልደታ ፖሊስ መምሪያ 0115153760፣ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ 0111575059፣የካ ፖሊስ መምሪያ 0116183339፣ቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ 0115528044፣አቃቂ ፖሊስ መምሪያ 0114391437 በተጨማሪም ከየካ ክፍለ ከተማ የተካለሉ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና ከቦሌ ክ/ከተማ የተካለሉ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመረጃ መቀበያ ስልኮች ደውሎ በማሳወቅ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.