የሀገር ውስጥ ዜና

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከምርጫ ዝግጅት ጎን ለጎን የአረንጒዴ አሻራ ለማሳረፍ ዝግጅት ተደርጓል-አቶ ዳኜ ሂርጳሳ

By Meseret Demissu

June 20, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ   አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ።

በክፍለ ከተማው ከምርጫ ዝግጅት ጎን ለጎን የአረንጒዴ አሻራ ለማሳረፍ ዝግጅት መደረጉን የክፍለ ከተማው የአካባቢ ጥበቃና የአረንጒዴ ልማት ፅህፈት ሀላፊ አቶ ዳኘ ሂርጳሳ ገልጸዋል።

በዚህም 27 የመትከያ ጣቢያ ዝግጁ መደረጉንም ሀላፊው ተናግረዋል።

በክፍለ ከተማው ባሉት 178 የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች መሰራጨቱ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልል  26 እና 27 ሀላፊ አቶ ረቢራ ኡጋሳ÷ በምርጫ ጣቢያዎቹ 163 ሺህ 659 መራጮች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በክፍለ ከተማው 10 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወደደራሉም ነው የተባለው ።

በተጨማሪም 73 ለከተማ አስተዳደሩ ምክርቤት 10 ለተወካዮች ምክር ቤት  እጩዎች የሚወዳደሩ መሆኑን ሀላፊው ተናግረዋል።

በዙፋን ካሳሁን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!