Fana: At a Speed of Life!

በአራዳና በቦሌ ክፍለ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአራዳና በቦሌ ክፍለ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ተጠናቋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ 98 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉት ተገልጿል።
የክፍለ ከተማው የክልል ምርጫ ፅህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ገላው ÷ለምርጫው የሚያስፈልጉ አጠቃላይ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ለኮቪድ ጥንቃቄ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተሰራጭተዋል።
በክፍለ ከተማው ለክልል ም/ቤት ዘጠኝ የፖሎቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩም አስተባባሪው አቶ ሳሙኤል አክለው ነግረውናል።
በክፍለ ከተማው የምርጫ ክልል 2 / 14 አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሚልኪያስ ዳንዴሳ÷ በክልሉ 27 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ገልፀው÷ አስራ አንድ የፖሎቲካ ፖርቲዎችም ለህዝብ ተወካዎች ምክር ቤት እንደሚወዳደሩ ነግረውናል።
በክፍለ ከተማው የምርጫ ክልል 1/ 9 አስተባባሪ የሆኑት አቶ በለጠ መንግስቱም÷ በክልሉ 54 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ገልፀው 11የፖለቲካ ፖርቲዎችም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚወዳደሩ ነው የነገሩን።
ከየካ ክፍለ ከተማ ጋር በቅንጅት የሚካሄደውን የምርጫ ክልል 12 /13ን የሚያስተባብሩት አቶ አበራ ተሾመም በአራዳ ክፍለ ከተማ 29 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን እና 9 የፖለቲካ ፖርቲዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንደሚወዳደሩ ገልጸዋል።
በተያያዘ በቦሌ ክፍለ ከተማ ሁሉም ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸዉ ተገልጿል።
በክፍለ ከተማው 12 ፓርቲዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11 ፓርቲዎች ደግሞ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አጩዎቻቸዉን አስመዝግበው ይወዳደራሉ።
ከፍለከተማው በ172 የምርጫ ጣቢያዎች 199 ሺህ 451 መራጮችን ያስተናግዳል።
በትዝታ ደሳለኝና በይመር ዳውድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.