የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ በሁሉም አካባቢ የምርጫ ጣቢያዎች ተዳርሶ መጠናቀቁ  ተገለጸ

By Meseret Demissu

June 20, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የምርጫ ቁሳቁስ በሁሉም አካባቢ የምርጫ ጣቢያዎች ተዳርሶ መጠናቀቁን በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ ።

የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ መኳንንት መከተ ከደቂቃዎች በፊት ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደገለፁት÷ በነገው ዕለት ለሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁሶች በሁሉም የክልሉ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰራጭቷዋል ብለዋል።

በክልሉ በ11ሺህ 464 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ የመስጠት ሂደት ይከናወናል ያሉት ሀላፊው የወቅቱን የአየር ሁኔታ ያገናዘበ ደረጃቸውን የጠበቁ ድንኳኖች ተዘጋጅተዋልም ነው ያሉት።

ጎን ለጎንም የኮሮና መከላከል ግብዓቶች በምርጫ ጣቢያዎች የደረሱ ሲሆን በነገው ዕለት መራጮች እየተጠቀሙ በዲሞክራሲያዊ ምርጫው ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

በክልሉ ከሰባት ሚሊየን በላይ ህዝብ የመርጫ ካርድ ያወጣ ሲሆን ከዚህ 46 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!