Fana: At a Speed of Life!

6ተኛዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ በራያ ቆቦ ወረዳ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)6ተኛዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ በራያ ቆቦ ወረዳ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን የራያ ቆቦ የምርጫ ክልል አስተባባሪ ተናገሩ።
ከህግ ማስከበር ጋር በተያያዘ ስጋት የነበረባቸው ለትግራይ ክልል አዋሳኝ የሆኑ ቀበሌዎች ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲመርጡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።
በዚህም ከአካባቢ ሚንሻ ጀምሮ በተዋረድ ያሉ የፀጥታ መዋቅር በጋራ እየሰሩ መሆናቸዉን የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ ሰሎሞን ደርበዉ ተናግረዋል።
የራያ ቆቦ ከተማ ኗሪዎች በበኩላቸው÷ ምርጫዉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን ሆነን እንሰራለን ብለዋል።
በራያ ቆቦ የምርጫ ክልል 150 የምርጫ ጣቢያዎች ሲኖሩ÷ 88 ሺህ ህዝብ በመራጭነት መመዝገቡም ተገልጿል።
የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተም ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የተዳረሰ ሲሆን 6 የፖለቲካ ፖርቲዎች በምርጫ ክልሉ ይወዳደራሉ ተብሏል፡፡
በኢሳያስ ገላዉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.