Fana: At a Speed of Life!

የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የያዙ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው በተገኙባቸው የምርጫ ክልሎች ነገ ምርጫ አይካሄድም

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የያዙ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው በተገኙባቸው የምርጫ ክልሎች በነገው ዕለት ምርጫ እንደማይካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

እነዚህም በአማራ ክልል ደምቢያ እንዲሁም ተሁለደሬ 1 እና 2፣ በኦሮሚያ ክልል ነጌሌ እና ግንደበረት የምርጫ ክልሎች መሆናቸውን የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

ቦርዱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በአማራ ክልል ደምቢያ እና ተሁለደሬ 1 እና 2፣ የምርጫ ክልሎች የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የያዙ ሰማያዊ ሳጥኖች በመከፈታቸው ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ግንደበረት የምርጫ ክልል የአስፈጻሚዎች እጥረት እንዲሁም ነጌሌ ላይ የግል እጩ ተወዳዳሪ ባቀረቡት ቅሬታ መሆኑን ተናግረዋል።

በደቡብ ክልል ስቄ 1 እና 2 ተመሳሳይ ችግር ቢከሰትም ሰማያዊ ሳጥኖች ሳይከፈቱ የመሰንጠቅ ችግር ብቻ ያጋጠመ በመሆኑ በቦታው ያሉ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈራርመው ምርጫው በአካባቢው እንዲካሄድ ተወስኗል።

በነገው ዕለት ድምፅ የሚሰጡ መራጮች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት አሰራር መዘርጋቱንም ወይዘሪት ሶሊያና ተናግረዋል።

ለዚህም በየድምፅ መስጫ ጣቢያው 3 አባላት ያሉት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ተዋቅሯል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በተጨማሪም በ778 ነፃ የስልክ መስመር መራጮች ቅሬታቸውን መግለፅ እንደሚችሉ ቦርዱ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.