Fana: At a Speed of Life!

“እመርጣለሁ አረንጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ“ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር “ እመርጣለሁ አረንጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ“ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር  ዝግጅት መጠናቀቁን አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 በሚካሄደው 6ኛው ብሄራዊና ክልላዊ ምርጫ “ እመርጣለሁ አረንጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ “ በሚል ታላቅ ሀሳብ ሁሉም መራጭ ችግኝ በመትከል ኢትዮጵያን እንድያለብሳት ጥሪ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ምርጫ በሚካሄድባቸው ክልሎችና ምርጫ ጣቢያዎች ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

ለዚህ ልዩ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ከፌዴራል እስከ ወረዳ ያለው የአረንጓዴ አሻራ ልማት አስተባባሪና ቴክኒክ ኮሚቴ እንዲመራው ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

በሁሉም ወረዳና ቀበሌ የሚሰሩ የግብርና ልማት ባለሙያዎች ሂደቱን ለመምራትና ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ተሰማርተዋል ተብሏል፡፡

ሰኔ 14 ቀን ምርጫ የሚካሄድባቸውንና በአሁኑ ወቅት ለችግኝ ተከላ በቂ ዝናብ ያላቸውን አካባቢዎች ለይቷል፡፡

መራጩ ህዝብ ጥሪው እንዲደርሰው እየተደረገ  መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሰኔ 14 ቀን ምርጫ በሚካሄድባቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 23 ሺህ 780 ምርጫ ጣቢያዎች 24 ሚሊየን 159 ሺህ 952 መራጭ ህዝብ አረንጓዴ አሻራውን እንዲያኖር ለማድረግ የተከላ ቦታ ተለይቶ በቁጥር 116 ሚሊየን 361 ሺህ 051 ጉድጓድ በህዝብ በተለይም በወጣቶች ሰፊ ተሳትፎ የተቆፈረ ሲሆን÷ በቁጥር 117 ሚሊየን 62 ሺህ 046 ጥራታቸው የተረጋገጡ ችግኞች ለየምርጫ ጣቢያዎች ወደ ተዘጋጀው መትከያ ቦታ ቀርቧል፡፡

በአፈጻጸም ደረጃ የኦሮሚያ ክልል የዲሞክራሲ መሰረት የሚጣልበት ስድስተኛውን ብሄራዊና ክልላዊ ምርጫ ለማሰብ እያንዳንዱ መራጭ 6 ችግኝ እንደሚተከል ታሳቢ በማድረግ 80,578,477 ጉድጓድና 83,768,118 ችግኝ፣ የአማራ ክልል 13,911,929 ጉድጓድና 13,911,929 ችግኝ፣ የደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች ክልል 6,649,792 ጉድጓድና 8,521,438 ችግኝ፣ ሲዳማ 7,585,607 ጉድጓድና 7,585,607 ችግኝ አዘጋጅተዋል፡፡

ከከተሞች ከፍተኛውን አዲስ አበባ 2,800,000 ጉድጓድና 2,800,000 ችግኝ አዘጋጅቷል፡፡ በተለየ መንገድ ደግሞ የሀረሪ ክልል ምርጫ የማይካሄድበት ቢሆንም በእለቱ የክልሉ መራጮች አረንጓዴ አሻራ በማሳረፍ ሀገራዊ በሆነ ታላቅ ሀሳብ ለማሳተፍ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን የከተማው ነዋሪ በደጃፉ እስከ ሶስት ችግኝ በድምሩ 100,000 ችግኝ ለመትከልና የገጠሩ ነዋሪ ደግሞ የችግኝ ጉድጓድ በመቆፈርና በሁለት በተመረጡ ቦታዎች በጋራ በመሆን ችግኝ የሚተከልበት መርሃ-ግብር ተዘጋጅቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.