Fana: At a Speed of Life!

ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ለምርጫው ፍሬያማነት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ ነው-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም ባለ ድርሻ አካላትና የፀጥታው ሃይል ለምርጫው ፍሬያማነት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
ምክትል ከንቲባዋ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን አዲስ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ እየተለማመዱ መሆናቸው እዉን እየሆነ ነዉ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው።
ሁሉም ባለ ድርሻ አካል እንዲሁም የፀጥታው ሃይል ለምርጫው ፍሬያማነት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሲወጡ ተመልክተናል ነው ያሉት።
ሁሉም እንቅስቃሴ በፍጹም የሰላምና የይቻላል ድባብ ዉስጥ እየተከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች፡፡
በዚህ ታሪካዊና ለአገራችን ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ስርዓት መሰረት በሚጥለው 6 ኛዉ አገር አቀፍ ምርጫ ላይ በተፎካካሪነት እና በመራጭነት ለምትሳተፉ ሁሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም “ለመላው ዓለም የጀመርነውን አዲስ የፖለቲካ እሳቤ በገሀድ እናሳያለን ፤ በችግኞቻችን ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናለብሳለን!” ሲሉ አስፍረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.