Fana: At a Speed of Life!

በጅማ እና አጋሮ ከተማ ድምጽ መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ እና አጋሮ ከተማ 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ ድምጽ መስጠት ተጀመረ፡፡

የድምጽ መስጠት ሂደቱ የተጀመረው የምርጫ ታዛቢዎች የጽምፅ መስጫ ኮሮጆዎችን ባዶ መሆናቸውን ከተመለከቱ በኋላ ነው ፡፡

የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎችም ቀድመው 11 ሰዓት ከ30 በምርጫ ጣቢያ የተገኙ ሲሆን፤ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ድምጽ መስጠት ጀምረዋል።

ነዋሪዎቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየትም “ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታችንን የምናረጋግጥበትና የሚወክለንን የምንመርጥበት በመሆኑ ማልደን የምርጫ ጣቢያ ተገኝተናል” ብለዋል።

በሙክታር ጠሃ እና አፈወርቅ አለሙ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.