የሀገር ውስጥ ዜና

በደብረ ብርሀን ከተማ 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተጀመረ

By Meseret Awoke

June 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሀን ከተማ 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተጀምሯል።

ታዛቢዎች የጽምፅ መስጫ ሳጥን ባዶ መሆኑን ከተመለከቱ በኋላ ነው ምርጫው የተጀመረው።

የከተማዋ ነዋሪዎች ሌሊት 10 ሰዓት በምርጫ ጣቢያ የተገኙ ሲሆን ድምጻቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ነዋሪዎቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየትም “ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታችን የምናረጋግጥበት በመሆኑ በጠዋት የምርጫ ጣቢያ ተገኝተናል” ብለዋል።

መራጩ ወረፋውን ጠብቆ መምረጥ ጀምሯል ሁሉም የምርጫ ካርድ የያዘ መራጭ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በደብረ ብርሀን ከተማ በ105 የምርጫ ጣቢያዎች ነው የድምጽ አሰጣጡ የተጀመረው።

በአላዩ ገረመው እና ሳምራዊት የስጋት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!