የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የምርጫ ሂደቱን እየታዘበ ነው

By Tibebu Kebede

June 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ የተመራው የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የምርጫ ሂደቱን እየታዘበ ይገኛል።

የህብረቱ ታዛቢዎች በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የምርጫ ክልል 21/22 ምርጫ ጣቢያ 4 እና 5 የምርጫ ሂደቱን በመታዘብ ላይ ናቸው።

በዘንድሮው ምርጫ 45 ሺህ የአገር ውስጥ ታዛቢዎች በታዛቢነት የሚገኙ ሲሆን 45 አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችም እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!