የሀገር ውስጥ ዜና

የባልደራስ ፖርቲ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የህዝብ ተወካዮች ተመራጭ ልጅ ጌታቸው ተድላ ድምጽ ሰጡ

By Tibebu Kebede

June 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የባልደራስ ፖርቲ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የህዝብ ተወካዮች ተመራጭ ልጅ ጌታቸው ተድላ በአራዳ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 2/14 ወረዳ 08 ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል፡፡

ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ህዝቡ ድምፁን ሲሰጥ መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡

ይህም ህዝቡ በምርጫ ላይ ያለውን እምነት የሚያመለክት ነው ብለዋል፡፡

ለመራጭነት ብቁ የሚያደርገውን ካርድ ወስዶ እስካሁን ያልመረጠው ቀሪው ህዝብም የሱ አንድ ድምፅ ዋጋ እንዳላት ተረድቶ ድምጽ እንዲሰጥ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!