በቻግኒ የምርጫ ክልል ጓንጓ ወረዳ በሚገኙ ስጋዲ የምርጫ ጣቢያ አርሶ አደሮች ድምፅ እየሰጡ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻግኒ የምርጫ ክልል ጓንጓ ወረዳ በሚገኙ ስጋዲ የምርጫ ጣቢያ አርሶ አደሮች ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
ወቅቱ እርሻ የሚለሰለስበትና የበቆሎ እንክብካቤ የሚከናወንበት ቢሆንም ድምጻችን ያላት ዋጋም የቀጣዩን ህይወት የምትወስን በመሆኗ ድምጻችንን ልንሰጥ መጥተናል ብለዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው አርሶ አደር ረታ ገነት ከጧቱ 12 ሰአት እስከ 5 ሰዓት እርሻቸው ጋር ቆይተው አሁን ድምፅ ለመስጠት ምርጫ ጣቢያ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!