በቻግኒ የምርጫ ጣቢያ ወ/ሮ ውበቴ ወርቁ ድምጽ ለመስጠት መጥተው የሴት ልጅ እናት ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻግኒ የምርጫ ክልል ወልደኋይታ ምርጫ ጣቢያ ወይዘሮ ውበቴ ወርቁ ድምጽ ለመስጠት መጥተው የሴትልጅ እናት ሆነዋል።
ድምጼን ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያው ስመጣ ምንም የህመም ስሜት አልነበረኝም ያሉን ወይዘሮ ውበቴ ካርዴ ለማስገባት ስገባ የህመም ስሜት ተሰማኝ ብለውናል።
ወዲያውም ወደ ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሁስፒታል ገብቼ ልጄን ወልጃለሁ በዚህም ሁለት ደስታን አስተናግጃለሁ ሲሉ ስሜታቸውን አጋርተውናል።
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!