የሀገር ውስጥ ዜና

በካፋ ዞን በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የገጠመውን የምርጫ ወረቀት እጥረት  ለማስተካከል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

By Meseret Demissu

June 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በካፋ ዞን በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ወረቀት እጥረት  መከሰቱን ጣቢያችን ባደረገው ቅኝት አረጋግጧል።

የምርጫ ወረቀት እጥረቱን  ለማስተካከል ትርፍ የምርጫ ወረቀት ከያዙ ጣቢያዎች እየተወሰደ በመሰራጨት ላይ መሆኑን የካፋ ዞን የምርጫ ማስተባበሪያ ሃላፊ አህመድ አባተማም ለጣቢያችን ገልጸዋል።

ጣቢያችን በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ባደረገው ቅኝት የመራጩ ማህበረሰብ አሁንም  ረጃጅም  ሰልፍች እንዳሉ እና  የምርጫ ወረቀት እጥረት ግን አሁንም በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች እንዳለ ተመልክቷል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!