የሀገር ውስጥ ዜና

ቦርዱ በሀዋሳ የተከሰተውን የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ለማስተካከል ጥረት ማድረጉን አስታወቀ

By Tibebu Kebede

June 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዋሳ ከተማ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የተከሰተውን የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ለማስተካከል ጥረት መደረጉን በምርጫ ቦርድ የሀዋሳ ከተማ ምርጫ ክልል አስታወቀ፡፡

የተላከው ወረቀት ሙሉ አለመሆኑን ተከትሎ ችግሩ መከሰቱን የገለፁት የከተማው ምርጫ ክልል አስተባባሪ ወይዘሮ ገነት ማርቆስ ከቀን ጀምሮ በአብዛኛው አካባቢ እጥረት ተከስቶ ነበር ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ሙሉ ለሙሉ እጥረቱን ሊቀርፍ የሚችል የቁሳቁስ አቅርቦት መከናወኑን ገልፀዋል፡፡

ድምጽ መስጫ ወረቀቱ በፍጥነትና ከበቂ በላይ ከአዲስ አበባ በሄሊኮፕተር መጥቶ በየምርጫ ጣቢያዎቹ እየተሰራጨ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

ህዝቡም በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!