የሀገር ውስጥ ዜና

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ እስከ ምሽቱ ሶስት ሰአት ተራዘመ

By Tibebu Kebede

June 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እስከ ምሽቱ ሶስት ሰአት ድረስ መራዘሙን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ በተለያየ ምክንያት በድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይ የተፈጠሩ መዘግየቶችን ተከትሎ ድምጽ አሰጣጡ መራዘሙን አስታውቋል፡፡

በዚህም እስከ አመሻሹ 12 ሰአት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ድረስ የገቡ መራጮች እስከ ምሽት ሶስት ድረስ ድምጽ እንዲሰጡም ወስኗል፡፡

መራጮችም ሂደቱ መራዘሙን ተገንዝበው በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ እንዲሰጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!