Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞንና በአሰላ ከተማ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማውና በዞኑ በ18 የምርጫ ክልሎችና በ1ሺህ 434 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ተሰጥቷል፡፡
የዞኑ የምርጫ አስተባባሪ አቶ መኮንን ሲሳይ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሂደቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ምርጫ ያጠናቀቁ ጣቢያዎች እንዳሉ ሆነው እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስም መራጮች የሚያስተናግዱ ጣቢያዎች አሉ ብለዋል፡፡
ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት አስተያያየታቸው የሰጡ የምርጫ ታዛቢዎች ሂደቱ ግልፀኝነት የተስተዋለበት ነው ብለዋል፡፡
በተያያዘም 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እየተጠናቀቀ መሆኑን የአርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማደን ገረሙ አሰፋ የፀጥታ ሀይሉ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራቱ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል አግዟል ነው ያሉት፡፡
ኤርሚያስ ቦጋለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.