Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ምርጫው በሰላም እየተካሄደ ነው-ፖሊስ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ምርጫው በሰላም እየተካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ ያለስጋትና በነፃ ድምፁን መስጠት እንዲችል የምርጫ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን በመመደብ አስፈላጊውን ፍተሻና ቁጥጥር እያረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም ህብረተሰቡ ፣ ምርጫ ቦርድ ፣ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እያደረጉት ላለው ትብብር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃት እየተወጡ ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡
በመሆኑም ትብብሩ የምርጫው ሂደት እስከሚጠናቀቅ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል ፡፡
ምርጫ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቅ እንዲሁም የምርጫ ቦርድ በሚወስነው መሰረት ኃላፊነቱን በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑ መገለፁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.