Fana: At a Speed of Life!

በአሶሳ የመራጭ ካርድ የቀደደ ግለሰብ ተቀጣ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የመራጭ ካርድ በመቅደድ የተከሰሰ ግለሰብ በገንዘብ ሲቀጣ በተመሳሳይ ጥፋት የተገኘ ሌላ ግለሰብ ደግሞ በቁጥጥር ስር ውሎ ውሳኔው ለነገ እየተጠበቀ መሆኑ ተገለጸ።

የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ቡሽራ አልቀሪብ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ግለሰቡ የተቀጣው በከተማው ወረዳ ሁለት ውስጥ የጓደኛውን ምርጫ ካርድ ቀምቶ በህዝብ ፊት በመቅደዱ ነው፡፡

የከተማው ወረዳ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ግለሰቡ የ1 ሺህ ብር ቅጣት እንደጣለበት ጠቅሰው፥ “ካርዱ የተቀደደበት ግለሰብ ከምርጫ ጣቢያ ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር ድምጽ እንዲሰጥ ተደርጓል” ብለዋል፡፡

ሌላው ግለሰብ ደግሞ የራሱን ምርጫ ካርድ በህዝብ ፊት መቅደዱን ኮማንደር ቡሽራ ጠቅሰዋል።

ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፥ ጉዳዩ ነገ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሚያገኝ አስታውቀዋል፡፡

ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በአሶሳ ከተማ በሠላም ሲካሄድ መዋሉን ኮማንደር ቡሽራ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.