Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን እናልብስ የአዲስ አበባ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያን እናልብስ የአዲስ አበባ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ይህ መርሃ ግብር ከምርጫ ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ድምፅ በተሰጠበት ማግስት የምናባክነው ደቂቃ የለንም በሚል ወደዚህ መግባት ተችሏልም ብለዋል።

ይህንን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ኢትዮጵያውያን በትብብር ልናከናውነው ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ለዓለም ህዝብ አዲስ ታሪክ መስራት እንደሚችሉ ማሳየታቸውንም አንስተዋል።

በትላንትናው ሀገር አቀፍ ምርጫ እኛ ኢትዮጵያዊን ለዓለም ምን ማድረግ እንደምንችል አሳይተናል ያሉት ደግሞ የሠላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ናቸው።

ለዚህም እያንዳንዱ ግለሰብ ይህን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በአዲስ አበባ የተጀመረው ኢትዮጵያን እናልብስ መርሃ ግብር ሀገርን ለማልበስ የተጀመረውን ራዕይ ለማሳካት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ዴሞክራሲን ለመትከል ያደረግነውን ርብርብ አረንጓዴ አሻራን ለማልበስም በሚደረገው ጥረት መረባረብ ይገባል ብለዋል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ባለሃብቶች ተገኝተዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በአዲስ አበባ 14 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን በመድረኩ ላይ መገለጹን ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.