በካፋ ዞን፣ ወላይታ ዞን እና በየም ልዩ ወረዳ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በካፋ ዞን፣ ወላይታ ዞን እና በየም ልዩ ወረዳ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ እየተደረገ ይገኛል።
በካፋ ዞን አብዛኞቹ የድምፅ ውጤት ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት እየተለጠፈ ነው።
በተመሳሳይ በወላይታ ዞን ሁምቦ ጠበላ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ተገልጸው፥ ህብረተሰቡም ጊዜያዊ ውጤቶችን እየተመለከተ እንደሚገኝ ደሬቴድ ዘግቧል።
በተጨማሪም በየም ልዩ ወረዳ በሳጃ ከተማ ከማለዳው ጀምሮ ጊዜያዊ ውጤት በተለጠፈባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ዜጎች ውጤቱን እየተመለከቱ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!