በመቱ እና በባሌ ሮቤ ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት እየተገለጸ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በመቱ እና በባሌ ሮቤ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ድምፅ ውጤት እየተገለጸ ይገኛል።
በመቱ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ድምፅ ውጤት እየተገለጸ ሲሆን፥ ህብረተሰቡም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ውጤቱ እየተመለከተ ነው።
በኢሉ አባቦራ ዞን በሁሉም አካባቢዎች ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ነጋሽ አስታውቀዋል።
በባሌ ሮቤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት የተገለጸ ሲሆን፥ በአብዛኞቹ ጣቢያዎች ግን አሁንም ቆጠራው አልተጠናቀቀም ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!