የሀገር ውስጥ ዜና

ምርጫው የጎላ የፀጥታ ችግር ሳያጋጥም በሰላም መጠናቀቁን የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለጸ

By Tibebu Kebede

June 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ካለምንም የጎላ የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር አደሬ ቶላ በሰጡት መግለጫ÷ የተለያዩ አካላት ምርጫውን ለማሰናከል ቢሞክሩም በህዝቡና በፀጥታ አካላት ትብብር ሀሳባቸው መክሸፉን አንስተዋል፡፡

ለዚህም ከፀጥታ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር የተደረገ ቅድመ ምርጫ ዝግጅት ስራ ጉልህ ሚና መጫወቱን ነው የገለፁት።

ስለሆነም የምርጫው ሂደት በታሰበው ልክ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቅ ተችሏል ነው ያሉት ሃላፊው።

ህዝቡ ላሳየው የሰላም ወዳድነት ትብብር ምስጋናቸውን ያቀረቡት ኮማንደር አደሬ ቶላ÷ ከምርጫው በኋላም ሰላሙን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

ይድነቃቸው ኃይለማርያም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!