Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ሳምንት 38 ያህል ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአንድ ሳምንት 38 ያህል ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

በተያዘው ወርም ከሰኔ 5 እስከ 11 ድረስ ከ91ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገልጿል።

እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን÷ የገቢ ኮንትሮባንድ 89 ሚሊየን 569 ሺህ 588 ብር ሲሆን የወጪ ኮንትሮባንድ ደግሞ 2 ሚሊየን 205 ሺህ 154 ብር ግምት እንዳላቸው ተመላክቷል፡፡

ከተያዙት ኮንትሮባንድ ቁሶች መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ እና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን 38 ያህል ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.