የሀገር ውስጥ ዜና

መራጮች የድምጽ ውጤቱ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ እስከሚደረግ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ተጠየቀ

By Tibebu Kebede

June 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በምርጫ ህጉ መሰረት ውጤቱ በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል፡፡

የምርጫ ውጤትን አስመልክቶ ዜጎች ከሌሎች ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡም ነው ያሳሰበው፡፡

ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች በከፍተኛ ንቃትና ትዕግስት ድምጻቸውን ለመስጠት ላደረጉት ተሳትፎም ቦርዱ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!