ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 5ኛ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን በይፋ አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገነባውን 5ኛ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በይፋ ስራ አስጀመሩ።
ማዕከሉን በይፋ ስራ ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፥ ‘‘ ትጋታችን ይቀጥላል፤ እርስበእርስ በመረዳዳት እና በመተሳሰብ ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ሲጠናክር ታሪክ እንሰራለን’’ ብለዋል።
አንድነት እና መተባበሩ በቀጣይ በልማቱም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ ወገኖቻችን መርዳት እና ተጠቃሚ ለማድረግ መልካም ልብ እና መተሳሰብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ዛሬም ሆነ ከዚህ ቀደም የተከፈቱት የምገባ ማዕከላት አቅመ ደካሞችን፣ እናቶች እና አረጋውያንን ከመመገብ ባሻገር የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕረስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዛሬው ዕለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራውን በይፋ የጀመረው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የተገነባ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ጠለፋ መድህን አክሲዮን ማህበር የ5 ሚሊየን ብር፣ ሮሃ ሜዲካል ካምፓስ ሔልዝ ፋውንዴሽን 1ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!