Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ያለምንም እንከን ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ የተካሄደው 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የድሬዳዋ ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዚያድ ያሲን ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ÷በአስተዳደሩ በከተማና በገጠር በ265 የምርጫ ጣቢያዎች የተካሄደው ምርጫ ያለምንም ችግር በሠላም መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

ምርጫው በተካሄደበት ወቅት በገጠር በሚገኙ 3 የምርጫ ጣቢያዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻ የሚያገለግሉ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች በመምጣታቸው ምክንያት ድምፅ ያልተሰጠባቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይ በሌሎች ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቶች በተወሰነ መልኩ እጥረት ቢያጋጥምም ከመጠባበቂያ በመሙላት ምርጫው እንዲካሄድ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

ኮተኒ መንገድ ላይ በተባለው ንኡስ ምርጫ ጣቢያ የህዝብ ተወካዮችም ለአስተዳደሩ ምክር ቤት የድምፅ መስጫ የመጡት ወረቀቶች የተሳሳቱ በመሆናቸው ምርጫው እንዳልተካሄደ በማንሳት ÷ጉዳዩን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማሳወቅ ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይ ምርጫው በተካሄደባቸውና የድምፅ ቆጠራ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ለመራጩ ህዝብ ጊዜያዊ ውጤት እየተገለፀ እና የምርጫ ቁሳቁሱም ወደ ምርጫ ክልል እየተጓጓዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለምርጫው ስኬታማነት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የፀጥታ አካላት፣ ለአስተዳደሩ ማህበረሰብ እና ወጣቶችም ምስጋና አቅበዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.