የሀገር ውስጥ ዜና

ትናንት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ባልተጠናቀቀባቸው ቦታዎች ላይ ዛሬ ድምጽ እየተሰጠ ነው

By Tibebu Kebede

June 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸውቦታዎ በዛሬው ዕለት ድምጽ የመስጠቱ ሂደት ቀጥሎ እየተካሄደ መሆኑን የምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም በሲዳማ ክልል በሁሉም ምርጫ ክልሎች ከጠዋቱ 5 ሰአት ጀምሮ የድምጽ አሰጣጡ ሂደት የቀጠለ ሲሆን÷ በዛሬው እለትም የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

በጋምቤላ ክልል ባሉ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ተቋርጦ የነበረው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው እለት ይጠናቀቃልም ነው የተባለው።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለት ምርጫ ክልሎች ያለው ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ለጊዜው የቆመ ሲሆን÷ ቁሳቁሶች በሙሉ ታሽገው እንዲጠበቁ ቦርዱ ለአስፈጻሚዎች አሳውቋል።

ቦርዱ የሚቀጥለው የድምፅ አሰጣጥ ሁኔታ እና እስካሁን ያለውን ሂደት ገምግሞ የደረሰበትን ውሳኔ እንደሚያሳውቀም ጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!